top of page
  • Writer's pictureOLA Command

እራስንመከላከልየተፈጥሮመብትነው::

Afaan Oromo Version | English Version

(ከኦሮሞነፃነትሠራዊትከፍተኛውዕዝየተሰጠወቅታዊመግለጫ:)

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) በፋሺስታዊው የብልፅግና መንግሥትና አጋሮቹ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተቃጣበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመቀልበስ ብቻ ሳይሆን አብዛኛውን የኦሮሚያ ምድር ከጠላት ነፃ በማውጣት ህዝባዊ መሠረቱን እያረጋገጠ ይገኛል:: ይህ የሠራዊቱን ጥንካሬ ብቻም ሳይሆን የትግሉን ፍትሐዊነትም ያረጋገጠ ተግባር ነው::

ከኢምፓዬሪቱ የዘመናት የግዛት የፖለቲካ ቀመር የተቀዳውና ሥልጣንን በሀይል ይዞ በሀይል ብቻ የማስጠበቅ ፍላጎት ህዝባችንን ላልተገባ በደልና እልቂት የዳረገ ሲሆን ይሄው አባዜ ዛሬም ድረስ የህዝባችንን ሁለንተናዊ ህይዎት እያመሰቃቀለ ነው:: በቅርቡ ታሪካችንም ህዝባችን በትግሉ ያስወገደው የተዛባ የኢህአዴግ ፖለቲካና እሱንም ተከትሎ በውስጡ በተፈጠረው ሽኩቻ ምክንያት በለስ የቀናውና አራት ኪሎን የተቆጣጠረው ያረጀ ዘመን ህልመኛ ቡድን ምክንያት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍልና በሌሎችም አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ጦርነት ደም በገፍ እየፈሰሰ ነው:: ይህንንም እሳት የበለጠ ለማጋልና ህዝቡን በዚህ ጦርነት እሳት ለመማገድ መንግሥት ነኝ ባዩ ቡድን ትልቅ ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያነሳሳና የተሟላ የህዝብ ለህዝብ ጦርነት እንዲፈጠር የሚያደርግ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍቷል:: ወታደራዊ ሥልጠና የሌላቸውና ያልታጠቁ ህዝቦች "ሉአላዊነት ተደፈረ" በሚል የውሸት ትርክት ያለፍላጎታቸው እንዲዘምቱና የጥይት ማብረጃ እንዲሆኑም እያደረገ ይገኛል:: በቢሊዮኖች የሚገመት የህዝብ፣ የመንግሥትና የግል ንብረት ሆን ተብሎ እየወደመ ነው:: በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብም ከቄዬው እየተፈናቀለ ነው:: ሚሊዮኖችም ለረሀብ አደጋ ተጋልጠዋል::

ይህ የአንድን ጨፍላቂ አሀዳዊና ፋሺስታዊ ቡድን ዘለአለማዊ ሥልጣን ለማረጋገጥና የተስፋፊዎችን ጥግ የሌለው ህልም ለማሳካት የተከፈተ ጦርነት እየገፋ መጥቶ ዛሬ ወሎን ሙሉ በሙሉ ሊያዳርስ ተቃርቧል:: ላለፉት 400 አመታት የዘርና ማንነት ማጥፋት ጦርነት ሰለባ የነበረው የወሎ ህዝባችን በዚህ ጦርነት በቀጥታ ተሳታፊና ተጎጂ መሆኑም አይቀሬ ሆኗል:: የወሎ ኦሮሞ ህዝባችን መሬቱ የትግራይና የአማራ አጎራባች በመሆኑ ብቻም ሳይሆን እሱን የኔ ነው ብሎ የሚከላከልለት መንግሥት ስለሌለውና ራሱንና ቄዬውን ለመጠበቅ ሲባል በጦርነቱ በቀጥታ መሳተፉ የግድ ይሆናል:: በየትኛው ጎራ መሳተፍ እንዳለበት ህዝባችን ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ግን እርግጠኞች ነን::

የሚገርመውና የሚያሳስበው ጉዳይ ግን ተስፋፊው የአማራው ሀይልና ጨፍላቂው መንግሥት ህዝባችንን ከጎናቸው ለማሰለፍና እምቢ ካለም በሌሎቹም አካባቢዎች እንዳደረጉት በሀይል በመጠቀም ለማዝመት እየሄዱበት ያለው ርቀት ነው:: ይህ ሙከራ የህዝባችንን የምዕተ አመታት ታሪክ ያላገናዘበ ብቻ ሳይሆን ከአመትና ሁለት አመት በፊት የተፈፀመበትን ግፍ እንደረሳ አድርጎ ህዝባችንን መናቅ ነው:: ከነዚህ ሀይሎች ጎን መሰለፍ ማለት ትናንት በገዛ ቄዬው ላይ መጥቶ ሀገራችንን ለቃችሁ ወደወለጋ ግቡ እያለ የፈጀንን ተስፋፊ የአማራ ፋኖና ልዩ ሀይል ሀጢያቶች መርሳት ነው:: ከዚህ ሀይል ጋር ተሰለፉ ማለት ትናንት በሸዋ ሮቢት ከአምቡላንስ አውርደው በዚህ ሀይል በግፍ የታረዱ ንፁሀን ኦሮሞዎች ደም ላይ መሳለቅ ነው:: ከዚህ ሀይል ጎን መሰለፍ ዛሬ በቀውጢው ቀን እንደክብር በሚጠሩት ሽርጥ ለዘመናት ሽርጣም እያለ አንገት ላስደፋው ወራሪ ተስፋፊና ጨካኝ ሀይል መዋጋት ነው:: ከሁሉም በላይ ከዚህ አሀዳዊ ተስፋፊና ጨፍላቂ ሀይል ጎን ሆኖ መዋጋት ለዘመናት በደሙ ያስከበረውንና ግን ደግሞ በቅጡ ያልተተገበረውን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት መውጋት ነው::

ስለሆነም ማንነቱ በግፍ የተገፈፈውም ሆነ ማንነቱን በመራራ ትግሉ አስከብሮ ለመላው የኦሮሞ ህዛብ ኩራት የሆነው የወሎ ኦሮሞ ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በመቀናጀትና በራሱም በመደራጀት የሚከተሉትን እንዲገነዘብ/ እንዲፈፅም የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛው ዕዝ ያሳስባል::

1ኛ. ከላይ እንደጠቀስነው ማንም በኦሮሞነቱ የሚያምን ሰው በየትኛውም መልኩ ከአሀዳዊውና ጨፍላቂው የአማራና የብልፅግና ሀይል ጎን በመሰለፍ በዚህ ጦርነት እንዳይሳተፍ ህዝባችን ባለው ባህል ተጠቅሞ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን::

2ኛ. ህዝባችን በዚህ ጦርነት የሚገኘውንም ሆነ ከዚህ በፊት በእጁ ያለውን ማንኛውንም ትጥቅና ስንቅ ለራስና ሌላም መታጠቅ የሚችለውን በማስታጠቅ የራስን ህልውና ለማስከበርና ዘላቂ ነፃነታችንን ለመጎናፀፍ ለሚያደርገው ፊልሚያ እንዲጠቀም እንመክራለን::

3ኛ. በተሳሳተ መንገድ በአማራውና በብልፅግና ፋሺስታዊ ሀይል ውስጥ ያላችሁ የኦሮሞ ልጆች ይህ ጦርነት የተስፋፊዎችን ህልምና የግለሰብ ሥልጣንን ለማስፈፀምና ለመጠበቅ የሚደረግ ኢፍትሐዊ ጦርነት እንጂ የናንተንና የህዝባችሁን ዘላቂ ጥቅም የማያስጠብቅ መሆኑን ተረድታችሁ ወደ ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እና ወደ ህዝባችሁ በመቀላቀል ታሪካዊና ብሔራዊ ግዳጃችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብን በዚህ ኢፍትሐዊ ጦርነትም ባለመሳተፍ በዚህ ጦርነት በተፈፀሙ የጦርና ዘር ማጥፋት ወንጀሎች ከመጠየቅ እራሳችሁን እንድታድኑ እንመክራለን::

4ኛ. የታጠቃችሁ የአካባቢው የፀጥታ ሀይሎችም ጊዜው ከመርፈዱ በፊት ከነትጥቃችሁ በአካባቢው ላለው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን::

5ኛ. የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት ያካሄደው ትግልና የከፈለው መስዋእትነት ቋንቋህን የሚናገሩና ባንተ ስም እየማሉ ያንተ ነን የሚሉ ቃላባይ ግለሰቦችንና ቡድን ወደሥልጣን ለማምጣት ሳይሆን ህዝባችን ነፃነቱን ሀገራችን መሬቱ ሳይሸራረፍ እንዲከበር መሆኑን በመረዳት "እኛ ያንተ ነን: እነሱ ጠላት ናቸው" የሚለውን የታሪካዊና ስትራቴጂያዊ ጠላት ሽንገላ በተለመደው የህዝባችን ባህልና ጥበብ እንድታመክን ቢያንስ ጆሮ ዳባ ልበስ እንድትል ልናስታውስህ እንወዳለን::

6ኛ. የኦሮሞ ህዝብ ዛሬ የሚታገለው ባለፉት 30 አመታት የደረሰበትን ጭቆና ለመበቀል ወይም በነዚህ ዘመናት ያጣቸውን መብቶች ለመመለስ ሳይሆን የዛሬ 150 አመት ገደማ (የወሎ ህዝባችን ደግሞ ከዚህም በረዘመ ዘመን) ያጣውን የሀገሩ ባለቤትነትና ራሱን በራሱ የማስተዳደር ምሉዕና ተፈጥሮአዊ መብት ለመመለስ መሆኑን ህዝባችን አንዳችም ብዢታ ሊኖረው እንደማይገባ አጥብቀን እናሳስባለን:: እንዲሁም:-

7ኛ. አለምአቀፉ ማህበረሰብ የኦሮሞና ሌሎችም ጭቁን የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች የሚያደርጉት የነፃነት፣ የዲሞክራሲና የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የማረጋገጥ ትግል መሆኑን በመረዳት ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪ እናቀርባለን::

8ኛ. ገዢዎች የስልጣን እድሜያቸውን ለማርዘም ህዝቦችን ከህዝቦች ማጋጨት ዋናው መሣሪያቸው መሆኑን በመረዳት፣ በነፃነት እና በእኩልነት የሚያምኑ ሀይሎች በሙሉ በአንድነት በመቆም የየህዝቦቻችን ዘመናት የፈጀ ትግል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በድል እንድንቋጭ በጋራ የመቆምና የመተባበር ጥሪያችንን እናቀርባለን:: ህዝቦችም የምናደርገው ትግል የትኛውንም ህዝብ ኢላማ ያላደረገና ይልቁንም በተስፋፊነት ህልምና በስልጣን ጥም አንተን ከሌላው በማጋጨት እድሜውን ለማራዘም የሚሰራን ሥርአት እና መንግሥት በመጣል ህዝቦች በሰላም እና በፍቅር አብረው እንዲኖሩ የሚያደርግ ፍትሓዊ ሥርአት በቀጠናው ለመፍጠር መሆኑን እንድትረዱ እናስገነዛባለን::

9ኛ. ሁሌም እንደምንለው የዚህች ኢምፓየር ችግር የሚፈታው በመሣሪያ አፈሙዝ ሳይሆን ለዘላቂ መፍትሔ በመነጋገር እንደሆነ እናምናለን:: ይህ የሠለጠነ የጋራ ችግርን የመፍታት ስልት እንዳይተገበር ደንቀራ የሆነውና ከአባቶቹ እንደተማረው ጦርነትን ብቸኛ አማራጭ ያደረገው የብልፅግና ፋሺስታዊ ቡድን ለሰላም እንዲንበረከክ ሁለንተናዊ ግፊትና ተፅዕኖ በውስጥና በውጭ ሀይሎች እንዲደረግ ደግመን እናሳስባለን::

በመጨረሻም የኦሮሞና የሁሉም የሀገሪቱ ጭቁን ህዝቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን ተፈጥሮአዊ መብት ሳይሸራረፍ እስኪከበር፣ ህዝቦች ተደራጅተውና ያዋጣናል ባሉት መንገድ ጨቋኝና ጨፍላቂ ሥርአቶችንና መንግሥታትን መታገል ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው እያልን ህዝባችን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ ጠላቱን እና ወዳጁን ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ጠላትም ሆነ ወዳጅ እንዲያውቀው እንፈልጋለን::

ድል ለኦሮሞና ለጭቁን ህዝቦች!!! የኦነሠ ከፍተኛው ዕዝ ኦክቶበር 27. 2021

5 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page